ዋጊኖስ ወይም የደጋ አባሎ ባለጠጕር፣ ሥሩና ፍሬው ለደም ተቅማጥ መድኀኒት ይኾናል። ቅጠሉም ቀጥቅጦ በውሃ ዘፍዝፎ ብልትንና ዐይንን ፡ እንዳይነካ ተጠንቅቆ ገላን ቢቀቡት ከዕከክ ያድናል ። ሌላ ስሙ ጉፋ ይባላል ። [ነገር ስም] ትንሽ ቍጥቋጦ ዕንጨት የይፋት አባሎ ፍሬው ለቍስል የሚኾን።
ቊጥቋጡ ወይም ዛፉ እስከ ፯ ሜትር ድረስ ይበቅላል።
በከፊል እርጥበት ባላቸው ጫካዎች ወይም በወይና ደጋ በተፈጁ መስኮች ላይ በጣም ተራ ቊጥቋጥ ነው።
ጸጉሩ ተመልጦ አላድግ ላለ ለራሰ በረሀ የኑግና የዋጊኖስ ቅጠል በአንድነት ወቅጦ ጨምቆ ጠዋት ጠዋት ለሰባት ቀን ሳያቋርጡ መቀባት ተመልሶ ጸጉር እንዲበቅል ያደርጋል፡፡ ቅድመ ጥንቃቄ የዋጊኖሱን ቅጠል ነክቶ አይን መንካት የተከለከለ ነዉ፡፡ከጥንቷዊዉ የአባቶቻችን የህክምና መጽሐፍ ከዕፀ ደብዳቤ የተገኘ፡፡
የቆዳ ችግሮችንና፣ ቁምጥናን፣ ቁስሎችንም ለማከም፣ የተደቀቁት ቅጠሎች ወይም ዘሮች ከቅቤ ጋር ይቀላቀላል።
የሥሮቹና የፍሬዎቹ የተፈላ ልጥ በተቅማጥና ወባ ላይ ያክማል።
ቢጫ-ቀይ ፍሬዎቹ በከብት በተለይም በበግ ቢበላ ገዳይ መርዝ እንደ ሆነ ተብሏል።
የተክሉ መረቅ የከብቶችን ማበጥ ለማከም እንደ ጠቀመ ተብሏል።[1]
ዕከክን ለማከም፣ የዋጊኖስና የሽነት ቅጠል እና የጌሾ ዘር ተደቅቆ በቅቤ ለጥፍ ይለጠፋል።
የአባለዘር በሽቶችን ለማከም፣ የዋጊኖስ ዘርና የጤፍ ዘር በውሃ ተጋግሮ በለጥፍ ይለጠፋል።[2]
በፍቼ ወረዳ እንደ ተዘገበ፣ ለእከክ ወይም ለችፌ፣ ቅጠሉ ተደቅቆ ለ፫ ቀን በውሃ ውስጥ ከቆየ በኋላ እንደ መታጠቢያ ይጠቀማል። ለውሻ በሽታ ቅጠሉ በቀጥታ ይበላል፤ ለማስታወክ፣ የደረቀው ቅጠል እንደ ጢስ በአፍንጫ ይናፈሳል።[3]
በዘጌ እንደ ተዘገበ፦ ለ«ቡላድ»፦ የፍሬ ዱቄት በማር ፩ ሳምንት ተቡኮ ይበላል። ለችፌ፦ የልጥና የቅቤ ለጥፍ ይቀባል። ለተቅማጥ፦ የቅጠል ጭማቂ በጧት ይጠጣል። ለ«አህያ ኪንታሮት»፦ የፍሬው ዱቄት በወተት ለ፫ ቀን ይጠጣል። ለ«ሙሽሮ»፦ የሥሩ ዱቄት በማር ይጠጣል።።[4]
Brucea antidysenterica là một loài thực vật có hoa trong họ Thanh thất. Loài này được J.F.Mill. mô tả khoa học đầu tiên năm 1779.[1]
Brucea antidysenterica là một loài thực vật có hoa trong họ Thanh thất. Loài này được J.F.Mill. mô tả khoa học đầu tiên năm 1779.