ግሥላ (በባዮሎጂ ባለሞያዎች Panthera pardus በሚል ሮማይስጥ ሥያሜ የሚታውቀው) በእስያ፣ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኝ አጥቢ አውሬ ነው።
በእስያ የተገኘው ነብር የግስላ ቅርብ ዘመድ ሆኖ፣ በአነጋገር «ግስላ»ና «ነብር» የሚሉ ስሞች ሊለዋወጡ ይችላሉ።
የአንድ ጎልማሳ ግሥላ ክብደት ከ35 እስከ 80 ኪ.ግ ሲደርስ በርዝመት ከ90 ሴ.ሜ እስከ 1,60 ሜ.ና በአፍሪካ የሚገኘው ዘር እስከ 1,90 ሜ ይደርሳል ። ከመሬት እስከ ሆዱ ከ50 እስከ 70 ሴ.ሜ ቁመት ሲኖረው ጭራው ደግሞ እስከ 100 ሴ.ሜ ርዝማኔ ያሳያል ። ሴቲቱ ከወንዱ አነስ ትላለች ። በዱር ሲኖር እስከ 10 አመት እንደሚኖር ሲታወቅ በሰው ተይዘው ሲኖሩ እስከ 20 አመት እድሜ ያስመዘገቡ ግሥሎች አሉ።